
H.I.M. lobbied to unify Eritrea with Ethiopia from under British rule
Atse Qedamawi Haile Selassie seen cutting the tape on the boundary between Eritrea and Ethiopia on 3rd October 1952, to establish the federation. The Emperor was determined that Eritrea would be fully incorporated into Ethiopia.
DID YOU KNOW
One of the great achievements of Emperor Haile Selassie was that he lobbied the US and Europeans for the reunification of Eritrea with Ethiopia, which had remained under the British rule after the Italian defeat in 1941. With the blessing of the United Nations Eritrea was re-united with Ethiopia in 1952. Undoubtedly, Haile Selassie was skilled in diplomacy and was know for his restless efforts of campaigns against colonization in Africa.
True, H.I.M our great leader ..we Ethiopians are proud H.I.M. ! ታላቁ መሪ አፄ ኃይለ ሥላሴ ከሰሯቸው እጅግ በርካታ ሥራዎች መካከል ጥቂቶቹን እንመልከት። እነዚህ ተግባራት በአብዛኛው ኢትዮጵያ ውስጥ ካለመኖር ወደ መኖር ያመጧቸው ናቸው።
1. ዘመናዊውን ሕገመንግሥትን አሰርተዋል።
2. ዘመናዊውን የፍትሐብሔርና የወንጀለኛ መቅጫ ሕጎችን አሰርተዋል
3. ፓርላማን ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ መስርተዋል
4. ዘመናዊ የሃገር መከላከያ ሠራዊት አደራጅተዋል
5. የኢትዮጵያን አየር ኃይል መሥርተዋል
6. ብቸኛውን የኢትዮጵያን አየር መንገድ መሥርተዋል
7. የመጀመሪያውን ዩንቨርሲቲ መሥርተዋል
8. የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤትን ከፍተዋል
9. የብሔራዊ ቴአትር ቤትን ከፍተዋል
10. የአባይን ወንዝ ለመገደብ ጥናቱን አስጠንተው ቅድመ ዝግጅት አጠናቀዋል
11. የወንጂ መታሃራ ስኳር ፋብሪካን የአዲስ አበባ ሲሚንቶ ፋብሪካን እና ሌሎች በርካታ ፋብሪካዎችን ከፍተዋል
13. ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በብዙ የሃገሪቱ ክፍሎች እንዲከፈቱ አድርገዋል
14. የጥቁር አንበሳንና ሌሎችን ትላልቅ ሆስፒታሎች አሰርተዋል
15. ኤርትራን ከእናት ሃገሯ አዋህደዋል
16. በርካታ የአፍሪካ ሃገራትን በማስታረቅ ወደሰላም እንዲመጡ አድርገዋል
17. በርሳቸው አነሳሽነትና መሪነት የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን አቋቁመዋል ጽ/ቤቱም አዲስ አበባ እንዲሆን አድርገዋል። ለብዙ የአፍካ ሃገራት ከቅኝ ግዛት ነጻ መውጣትም ከፍተኛ ርዳታ አድርገዋል
18. በሊግ ኦፍ ኔሺን በመገኘት የአለም ህዝብ ፋሺስት ወራሪን እንዲቃወም ጥሪ አድርገዋል
19. በተለያዩ የአለም ሃገራት በመዘዋወር የኢትዮጵያን ክብር አጉልተዋል።
20. ለመጀመሪያ ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስና ሌሎች የጸሎት መጽሐፍት ወደ አማርኛ ተተርጉመው እንዲታተሙ አድርገዋል
21. የአክሱም ጽዮን ማርያምን ዘመናዊውን ሕንጻ ቤተክርስቲያን የደብረ ሊባኖስን ህንጻ ቤተክርስቲያን የቁልቢ ገብርኤልን ቤተክርስቲያን የአ.አን ቅድስት ሥላሴ ካቴድራልና ሌሎች በርካታ ቤተክርስቲያናትን አሰርተዋል
22. ትንኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤትን አሰርተዋል። የቅድስት ሥላሴን እና የቅዱስ ጳውሎስን መንፈሳዊ ኮሌጆችን አቋቁመዋል
23. በተለያዩ ደረጃ ያሉ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች በውጪም በሃገር ውስጥም እየተማሩ በሚመረቁ ምሁራን እንዲሰሩ አድርገዋል
24. ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያውያን ጳጳሳት ሆነው እንዲሾሙ አድርገዋል
25. ኢትዮጵያ የራሷ ሲኖዶስና ፓትርያርክ እንዲኖራት አድርገዋል
26. የኢትዮጵያን ብሔራዊ ባንክ እና ንግድ ባንክ አቋቁመዋል
27. ሰፋፊ የመንግሥት እርሻ ተቋማትን አቋቁመዋል
28. ብሄራዊ ፓርኮችን ከፍተዋል
29. የሬድዮ ጣቢያ አቋቁመዋል
30. ህሙማንን በየሆስፒሉ እየሄዱ በመጠየቅ ተማሪዎችን በየትምህርት ቤቱ በመሄድ በመጎብኘትና በማበረታታት አባታዊና የህዝብ መሪ ማለት ምን ማለት እንደሆነ በተግባር አሳይተዋል።
እንደርሳቸው ያለ መሪ ዳግም ለኢትዮጵያ እግዚአብሔር ያድላት።